Thursday, May 7, 2020

በኮሮና ዘመን እይታን ማስተካከል !!

 تصحيح المفاهيم في زمان الكورونا 

በኮሮና ዘመን እይታን (ግንዛቤን) ማስተካከል !! 


ሙሐመድ ዐብዳህ “ምእራባዊያን ዘንድ እስልምናን አይቻለው ሙስሊሞችን ግን አላየሁም።” ብሎ ተናገረ ፣ ሙስሊሞች ዘንድ ያላየሁትን እስልምናን ምእራባዊያን ዘንድ አየው ማለት ፈልጎ ነው። ይህ በሙስሊሞች ላይ ሲደረጉ ከነበሩ ጥላሸቶች አንዱ ነው።


ይህ አባባል በሚሊዮን የሚቆጠሩትን ሙስሊሞች አእምሮ አበላሽቷል ፣ ፊቶቻቸውን ወደ ምእራባዊያን እንዲያዞሩ አድርጎታል እነሱ በመጀመሪያም የአመለካከትና የአስተሳሰብ ሁሉንም የማታስቀርም ጦርነት በሙስሊሙ ኡማ ላይ ከፍተው እያሉ በዚህም ሳቢያ ሙስሊሞች ሞራላዊ ድክመት እንዲሰማቸው ሆነዋል። ለዚህም ነው ሙስሊሞች ከጥንት ጀምሮ የሚታወቁበት እና ምርጥ ህዝቦች የሆኑበትን የ“አልወላእ ወልበራእ” (ለአሏህ ብሎ መውደድ እና ለአሏህ ብሎ መጥላትን) ዐቂዳ የደም ስሩን ገመድ የተቆረጠው።


በዚህ ጉዳይ ላይ ዑለማዎች እና ዱዓቶች ቀንና ማታ ጥሪ እያደረጉ ብዙ ሰዎችም ላይሰሙ ጣቶቻቸውን በጆሮዎቻቸው ውስጥ አደረጉ ፣ጥሪውን ላለ መቀበል በልብሶቻቸውም ተከናነቡ ያለ ልክ መኩራትንም ኮሩ ፣ ተደናባሪዎችም ሆኑ ልክ አንበሳን ያየች ሜዳ አህያ መሰሉ። እኔም ለእነርሱ ይመሩ ዘንድ (ወደ እምነት) በጠራኋቸው ቁጥር ጣቶቻቸውን በጆሮዎቻቸው ውስጥ አደረጉ፡፡ ልብሶቻቸውንም ተከናነቡ፡፡ (በመጥፎ ሥራቸው ላይ) ዘወተሩም፡፡ (ያለ ልክ) መኩራትንም ኮሩ ።

በእዚህ ላይ እያሉ በአሏህ ቀደር ሆኖ ኮሮና ወረርሽኝ መጣ እነዚያ የተሸወዱት እና ኩራተኞቹ ማን እንደ ሆኑ ሊገልጽና በገሃድ ሊወጣ። ይህ ውድቅ ንግግር በሙስሊሞች ሀገር ላይ አስካሪ መጠጥ እንዲስፋፋ አድርጎታል ።


እውነታው ግን አንድም ቀን በምእራባውያን ዘንድ 'እስልምናን አልነበረም ሙስሊም ሳይኖር' ይህን ንግግር ያሰራጨው ምእራባውያን ህገመንግስታቸውን ተግባራዊ ያደርጋሉ ብሎ ተገንዝቦ ይሆናል።
ምእራባዊያን ብዙ ግዜ ያከብሩሃል የሚያከብሩት ሰው ስለ ሆንክ ሳይሆን ሀብታም ወይንም ድሎት ስላለህ ብቻ ነው።
ምእራባዊያን መንደራቸው ንፁህ ሆኖ ታገኛለህ ነገር ግን ከስርዓት-አጥ በዓላቸው በኋላ በግማታሙ መጠጥ(ኸምር) ይሞሉታል።
ምእራባዊያን ግላዊ ነገርህን ሊያከብሩ ይችላሉ ነገር ግን የሱ ጎሮቤት ሆነህ በረሃብ ብትሞት እራሱ ላንተ ትኩረት አይሰጡህም።
ምእራባዊያን አንተ የሆነ አደጋ ሲደርስብህ በትንሽ ነገር እንኳ አይረዱህም አንተ የግድ ፖሊስን ጠርተህ እንዲረዳህ ከልጠየከው በስተቀር ።
ምእራባዊያን ደጃፋቸው (ቤታቸው) ያለውን እንጨት ይንከባከቡታል ነገር ግን ከደሃ ሀገራት በሺዎች የሚቆጠሩትን እንጨቶች ነው የተጨፈጨፉት ።


ምእራባዊያን ልክ አየር ማረፊያቸው ስትደርስ ሞቅ ያለ አቀባበል ያደርግልሃል ሰው ስለ ሆንክ ሳይሆን ገንዘብ ስለ ምታመጣላቸው።
ምእራባዊያን ዘንድ ሁሉም ማስመሰል እና ማታለል ነው ስነ-ምግባር እና ሰውን ማክበር የተባለው እራሱ እንደዚያው ነው። 🚫
በርግጥም አይተናል ምእራባዊያን ለተራ ነገር ለሶፍት እንደሚገዳደሉ ፣ እንደውም ሶፍት ሁላ ይሰርቃሉ በዛ ላይ አንዱ ለአንዱ ይደብቅለታል ።

ምእራባዊያን ጋ ኮሮና እንዳይዛቸው ህፃናት እንዴት ከአባቶቻቸው እንደሚሸሹ አይተናል አንድአንድ ፈረንሳዊ ዶ/ር በ"TV5" ቀርቦ ሲናገር ኮሮና ከገባ ወዲህ እኔ ከመጣብኝ የአይምሮ ጭንቀት የተነሳ የስነ_ልቦና ሀኪም ጋ መሄድ እንዳለብኝ ይሰማኝ ነበር። ነገር ግን ዛሬ አንድ በጠና ታሞ በጣረሞት ላይ ያለ በሺተኛዬ ልጆቹን ለመጨረሻ ግዜ እንዲያቸው አምርሮ አልቀሶ ለመነኝ ከዚያም ፈቃደኛ ሆንኩለትና አብሮኝ ከሚሰራው ቡድን ጋ አንድ ክፍል አዘጋጀን እና ልጆቹ ጋ ደውዬ ኑ አባታችሁን እዩ ስላቸው ከልጆቹ የገጠመኝ መልስ ግን ጭራሽ ያልጠበቁት ነገር ነው "ልናየው አንፈልግም ኮሮና ያስተላልፍብናል" አሉኝ እኔም በልመና ላግባባቸው ብሞክር ጭራሽ ከጆሮዬ ላይ ስልኩን ዘጉብኝ ። ይህን ድንበር ያለፈ ጭካኔ ሳይ እኔ ራሴ የመጨረሻ ተናደድኩ ከስራም መሄድ አቆምኩ ። ትላንት እሮሯቸውን ስሰማ የነበሩ ህመምተኞቼ ዛሬ ሙታን ሲሆኑ ሳልሰማ እንቅልፍ እንዲወስደኝ ብቻ ባሁኑ ሰአት ስራ አቁሜ በስነ ልቦና ሀኪም በመታገዝ አለ የሚባል ከባድ መድሀኒት በመውሰድ ላይ እገኛለሁ" ብሎ ሲናገር ቃል በቃል ሰምቸዋለሁ።
ይህ ካየነው አንፃር ከብዙ ጥቂቱ ነው ኮሮና መጥቶ ክዳኑን የገለፀው ።

ምዕራባውያን ፊቶቻቸው በሀዘን የተሞላ፣ አስጠሊታ፣ ጥቁር ምንም አይነት ብርሃን የለለው ጨለማ ነው። ወዳጆቹ እነ ማሱኒዮች እና ኢልማንዮች በቻሉት አቅም አሳምሮ ማቅረብ ቢሞክሩም እንኳን ለነገሩ ኮሮና ግልጽ አድርጎታል!!

እስልምናን ተግባራዊ ማድረግ በላጭ ህዝብ ያደርጋል ብላችሁ ካመናችው ለምን ተግባራዊ አታደርጉትም ትክክለኛውን እስልምና በሀገራችው ላይ እንድሆን ?!
⚠️ሲቀጥል የትኛውን እስልምና ነው ምእራባውያን ዘንድ ያለው?
⚠️ተውሒድ አይታችዋል?
⚠️አሏህ እና መልእክተኛውን ሲወዱ አይታችዋል?
⚠️ሀያእ እና ጥቡቅነትን ተላብሰው አይታችዋል?
⚠️እስልምናን በቤተሰቦቻቸው ተግባራዊ ሲያደርጉ አይታችዋል? እስቲ ንገሩን ያያችሁትን እውነተኞች ከሆናችሁ
በጌታዋ የካደችን ህዝብ ከፊል ስነ-ምግባርን ስላሳመረች “ሙስሊም ሳይሆኑ እስልምናን አየሁባቸው” የሚል አካል እስልምና ምን እንደሆነ በጥቅል ሆነ በዝርዝር ምንም አልተረዳም። እስልምና መሰረቶች ያሉት ግንባታ ነው የመጀመሪያው እና ዋነኛው መሰረት ደግሞ ከአሏህ ሌላ በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም (ላኢላሀ ኢለሏህ) እና ሙሐመድ የአሏህ መልእክተኛ ነው ብሎ መመስከር ነው እነሱ ደግሞ መሰረቱን የላቸውም ።
ታላቁ ሸይኽ ዶ/ር ሰሊም አልሂላሊ ሐፊዘሁሏህ